+Development through joint effort!!

About HDA

የሀድያ ልማት ማህበር

አደረጃጀትና አሰራር አጭር ዳሰሳ

ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ፣ ዋና እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያሉት ሲሆን ቀደም ሲል በነበረው ማህበሩ መተዳደሪያ ድንብ፣ እንዲሁም በተሻሻለው ደንብ መሰረት የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ትልቁ የሥልጣና አካል ሲሆን የስራ አሰፈጻሚ ቦርድ ከጠቅላላ ጉባኤ ቀጥሎ ያለ የስልጣን አካል ሆኖ ይቀጥላል፡፡  ጠቅላላ ጉባኤ አባላት የማህበሩ መስራች አባላትና የክብር አባላት እንደሆኑና ከአሰራር አኳያ ጠቅላላ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ ጉባኤ እንደሚያደረግ መስከረም 26/2002 የጸደቀው ደንብ ይጠቅሳል፡፡ 

ልማት ማህበሩ በእስካሁኑ እንቅስቃሴው በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ ከዞኑ ውጭ በሃዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በአዲስ አበባ፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያሉት ሲሆን በወላይታ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሀደሮ ጡንጦ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ለመክፈት ከየአካባቢው የብሄረሰቡ ተወላጆች ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም እስካሁን ምላሽ እንዳልተሰጠ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከአሰራር አኳያ መስከረም 26/2002 ዓ/ም የተሻሻለ ህገ ደንብ፣ እንዲሁም ጥር/2008 የመተዳደሪያ ደንቡ እንደተሻሻለ ፣ ነሃሴ 2/1996 የጸደቀ የተሻሻለው የሰራተኞች አሰተዳደር መመሪያ፣ በ2008 ዓ/ም ተሸሽሎ የወጣ ድርጅታዊ መዋቅር (የዋና ጽ/ቤት መዋቅር እስከ 29 ሥራ መደቦች ያሉት ሆኖ የተቀረጸው) ፣ የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያው HDA Financial Policy በሚል የተዘጋጀ ማኑዋል የማህበሩ አደረጃጀትና አሰራርን ለመወሰን የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ናቸው፡፡     

የሰው ሀይል በአሁኑ ወቅት በዋና የማህበሩ ጽ/ቤትን 14 ሰራተኞች እንዳሉና ከእነዚህ ውስጥ 8ቱ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች መሆናቸው ይታወቃል፡፡  

የአደረጃጀትና አሰራር ለውጥ ማድረግ ያስፈለገበት ዋና ዋና ምክንያቶች የተቋም አቅም ማለት የሶስት አቅሞች ውህድ እማለትም የሰው ሀብት በዓይነት፣ በመጠን እንዲሁም የተቋሙን ተልዕኮና ተግባራት ማሳካት የሚያስችል ክህሎት፣ ዕውቀትና ቁርጠኝነት ያለው የሰው ሀብት፣ የተቋሙን ተልዕኮ ሊያሳልት የሚችል ድርጅታዊ መዋቅርና አደረጃጀት፣ እንዲሁም በተቋሙ የተዘረጋና ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አሰራር ያካትታል፡፡ የሀድያ ልማት ማህበር የማስፈጸም አቅም ክፍተት ዳሰሳ ጥናት ሰነድ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ማህበሩ የሰው ሀብት በዓይነትን በመጠን፣ ተልዕኮውን ሊያሳልት የሚያስችል አደረጃጀትና የአሰራር ክፍተቶች እንዳሉበት ያመላክታል፡፡

Projects